ፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስና የኩባው ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮ የሚያመሳስላቸው ነገር ምንድነው??
- አዳኙ ካሜራ

- Jan 6, 2019
- 2 min read
Updated: Jan 6, 2019
በአንድ ወቅት አንድ የጣልያን ጋዜጣኛ ጌታ ፊትአውራሪ አባ መላን እንዲህ በማለት ትጠይቃቸዋለች የጥያቄው መነሻ ይኸ ነው ልጅ እያሱ እየማገጡም አንድንድ ከኢትዮጲያ ነገስታቶች ወግ መአረግ ያፈነገጠ ነገር ያደርጋሉ ለምሳሌ ጫት ሲቅሙ ሲጋራ ሲያጨሱ የምኒሊክ ምርቶች የሆኑት መኳንት የጦር አበጋዞች ይንቃሉ አልፈው ተርፈውም በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ እስልምናን የሚያመለክት ፅሁፍ ፅፈው ለቱርክ መንግስት ይልካሉ እኔ እያሱ መለዋን ኢትዮጵያን ባለአሰልማት እያሱ አይደለሁም ይላሉ ሀረር ሄደው ጫት እየቃሙ አብረዋቸው የነበሩት ፊትአውራሪ ተክለዋሪያት እንዲህ ይሏቸዋል ልጅ እያሱ አልጋው ያለው ሸዋ ነው እዚህ ምን እንሰራለን ሲሏቸው ሸዋ ምን ያመጣል ከፈለግሁ ሽንቴን ልሽናበት አፍህን ክፈት ብለው ''አ'' በል ብለው አፉን ከፍቶ ይሰጠኛል በማለት ይመልሳሉ በዚህ ድርጊታቸው የተናደዱት የሸዋ መካንትና የጦር አበጋዙ ፊት አውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲኔግዴ መስከረም 17 ቀን 1909 ዓ/ም ልጅ እያሱን በሌሉበት የምኒሊክን ቃል አልጠበቁም በማለት ከስልጣን ወርደዋል በማለት ያውጁባቸዋል በዚህ ጊዜ አያቱ ምኒሊክ ያወረሱትን ስልጣን የሸዋ መካንት አዲስ አባባ ላይ ተሰብስበው ምን አገባቸውና ነው ልጄን ከስልጣን የሚያወርዱት በማለት ከደሴ ጦር አስከትተው አባታቸው ራስ ሚካኤል አሊ ይመጣሉ ጥቅምት 7 ቀን 1909 በደብረብረሃንና በአንኮበር መካከል ቶራ መስክ ላይ በተደረገ ጦርነት የሸዋ ጦር ከጥቅም ውጪ መሆን ሲጀምር የሸዋ ጦር መሪ በስለላና በብለሃታቸው የተመሰገኑት አባ መላ ፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲኔግዴ ለወሎው ራስ ሚካኤል አንድ ደብዳቤ ይፅፉላቸዋል መነው ጌታዬ የትልቅ ቤት አይደለም ይኸ ሁሉ ሰው እንዴት በከቱ ያልቃል እኔም ከድቼ እማጣለው ይጠብቁኝ በማለት ጥይትና ጠመጃ ጨምረው ይልኩላቸዋል እውነት የመሰላቸው ገራገሩ ራስ ሚካኤል እየጠበቁ እንዳለ ራስ ተፈሪ መኮንን የልጅ ልጃቸው የእቴጌ መነን ባላቤት የሆኑት ራስ ሚካኤል አማች እና ፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዴኔግዴ ጦርራቸውን አደራጅተው በጥቅምት17 ቀን 1909 ዓ/ም ሰገሌ ላይ በመግጠም ራስ ሚካኤል ተማርከው በሰንሰለት ታስረው ሸዋ አዲስ አበባ ይገባሉ ማራኪው ፊትአውራሪ የጀግና ምልክት የሆነውን የሰጎን ላባ ሰከተው በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ሸዋ ይገባሉ በዚህ ጦርነት በሸዋ በኩል 8ሺህ ሰው ሲሞት በወሎ በኩል 12 ሺህ ሰው ሞቷል የጣልያን ጋዜጠኛ በዚህ ጦርነት ምክነያት ኢትዮጵያን እርስበር ልታጨራርስ ፈልጋ አባ መላን እንዲህ በማለት ትጠይቃቸዋለች በሸዋና በወሎ መካከል ማን ነበር ጦርነቱን ያሸነፈው ትላቸዋለች አባ መላም ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ በሸዋና በወሎ መካከል ጦርነት የለም በወንድም አማች መካከል ግጪት ነበረ ጠርነት ግን የለም ሰላም ነው ለምን ሰለአደዋው አትጠይቂኝም ማን እንዳሸነፈ እነግርሻለው እኔው ሰለዋልኩበት ሰለተሳተፍኩበት እነግርሻለው ወሎና ሸዋ ወንድማች ናቸው በጣልያንና በኢትዮጵያ መካከል ግን አሸናፊና ተሸናፊ ነበረ ኢትዮጵያ አሸናፊ ጣልያን ተሸናፊ ነበረች በማለት ይመልሱላታል:: በሌላ ጊዜ ደሞ አንድ የጣልያን ጋዜጠኛ የኩባውን ፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮን በመንግስቱ ሀይለማሪያም ዘመን የሱማሊያ ፕሬዝዳንት የነበረው ሳያድባያሬ እስላም የረገጠው ሱማሌ የሰፈረበት ሁሉ ሱማሊያ ግዛት ነው በማለት በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ያውጃል በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት በኮለኔል መንግስቱ ሀይለማርያም መሪነት ጦርነር ታውጆ ሱማሊያ ትሸነፋለች ኩባም ድጋፍ ለኢትዮጵያ አድርጋ ነበረ ሌላ የለመደች የጣልያን ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ሱማሊያን ያሸነፈቻት ከባ ሰለረዳቻት ነው ይባላል እውነት ነው ብላ ፊደል ካስትሮን ትጠይቃለች ፕሬዝዳንት ካስትሮ ሲመልሱ እሱን ለምን እኔን ትጠይቂኛለሽ አያቶችሽን ቅድመ አያቶችሽን አባቶችሽን ብትጠይቂ የኢትዮጵያዊያን ክንድ እንዴት እንዳደቀቃቸው ኢትዮጵያውያን ምን አይነት ጀግናና ጀበደኛ እንደሆኑ ይነግሩሽ ነበረ በማለት ለጋዜጠኘዋ መለሱላት ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር!!




Comments