top of page

ሳያጣሩ ወሬ፣ ሳይገድሉ ጎፈሬ፤

  • Writer: አዳኙ ካሜራ
    አዳኙ ካሜራ
  • Jan 6, 2019
  • 2 min read

Updated: Jan 6, 2019

አክቲቪስት @Achamyeleh Tamiru ስለ ግንቦት7፣ ካሳ ከበደ፣ አበበ በለዉ አይነት ቀጣፊ በሰዉ ድል ዘፋኞች፣ በንፁሀን ደም ተሸላሚዎች የሚከተለዉን ፅፏል።

"ከቀጣፊ ወደ ቀጣፊ እየተሸጋገርን ነው. . .

የአማራና የኦሮሞ ልጆች በከፈሉት መስዕዋትነት እዚህ በተደረሰ [ለውጥ መጣ አላልሁም] አንድ ጥይት እንኳ ሳይተኩሱ ራሳቸውን እንደ ጀግና እየቆጠሩ የሕይዎት መስዕዋትነት ከከፍሉት የአማራና የኦሮሞ ልጆች በላይ አንቱ በሉኝ እያሉ ጉሮ ወሸባዬ የሚሉትን ነውር የማያውቁ ቀጣፊዎች ያገራችን ሰው ገና ጥንት እንዲህ ብሎ ያነውር ነበር፤

ሳያጣሩ ወሬ፣ ሳይገድሉ ጎፈሬ፤

ዛሬ ላይ ግን ሕዝብ ታግሎ ላሸነፈው ሳይገድሉ ጎፈረ የሚጭኑትን የሚያነውር ሰው የጠፋ ይመስላል። ኸረ ለመሆኑ ሕዝብ ታግሎ ላሸነፈ ጉሮ ወሸባዬ ምንድን ነው? በወያኔ የሰለቸን ነውረኛነት እንቃወማለት በሚሉ ሲደገም ዝም ተብለው የሚታዩ ለምንድን ነው? ጀግና ትርጉሙ ምንድን ነው? ጀግና ማለት ያሸነፈ ማለት አይደለምን? ማሸነፍ ቀርቶ ወደ ፍልሚ ሜዳ ያልገባው እንዴት እንደ ጀግና ተቆጥሮ የጀግና አቀባበል ይዘጋጅለታል? ይሄ ሕዝብ የበላውና የጠገበው ነውረኛ ሄዶ በራበውና ሁሉ ብርቁ ነውረኛ እየተፈራረቀበት እስከመቼ ሲታለል ይኖራል?

በሌላ በኩል ሕዝባችን ፋሽስት ወያኔን ያበሸቀ እየመሰለው የወያኔ ወኪሎች ሆነው የዘር ማጥፋት የፈጸሙትን ወንጀለኞችና እጃቸው የፊጥኝ ታስሮ ዳኛ ፊት መቅረብ የነበረባቸውን ነውረኞች ጥንግ ድርብ ካባ እያለበሰ የጀግና አቀባበል እያደረገላቸው ይገኛል!

ለአማራ ሕዝብ አንድም ቀን ጮኸው የማያውቁ ብቻ ሳይሆን አማራ መባልን ተጠይፈው በአውሮፓና በአሜሪካ በሞቀ ቤታቸው ተቀምጠው የወገናቸውን እልቂት በቴሌቭዥን መስኮት ሲመለከቱ የኖሩ፣ ዛሬ ግን ያ ምስኪን ገበሬ በሚከፍለው ግብር ከሚኖሩበት ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሙሉ የጉዞ ወጫቸው ተሸፍኖላቸው የሕወሓቱን ብአዴን አርማ ደረታቸው ላይ አንጠልጥለው «የአማራ ክልል ተወላጆች ምሁራን ስብሰባ» የተባለውን በብአዴን ስፖንሰር አድራጊነት የተዘጋጀ ጉባኤን ሲሳተፉ እያየን ነው።

እነዚህ ሕወሓት ለብአዴን የፈጠረውን አርማ ትናንትና በባሕር ዳሩ ግባኤ ደረታቸው ላይ አንጠልጥለው ብአዴንን ሲያጀግኑ እያየናቸው ያሉት ሰዎች ከአመታት በፊት እነ ጀኔራል ኃይሌ ባይከዳኝ፣ ጀኔራል አብይ አበበ፣ ጀኔራል ከበደ ገብሬ፣ ጀኔራል ይልማ ሽበሺ፣ ጀኔራል አሰፋ አየነ፣ ጀኔራል ደበበ ኃይለ ማርያም፣ ጀኔራል እያሱ መንገሻ፣ ጀኔራል ስዩም ገድለ ጊዮርጊስ፣ ጀኔራል ነጋ ተገኝ፣ ጀኔራል ጃገማ ኬሎን፣ ኮሎኔል ስምረት መድኃኔ፣ ሜጀር ጥበበ መንክር፣ ወዘተ በተፈጥሩበት አገር ውስጥ ዋናውን ስራቸውን [የአገር ዳር ድንበር መጠበቅን] ትተው ደመወዝ ለማስጨመር አዲስ አበባ የከተቱ ደም የተጠሙ እንደ ኮልኮሌው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አይነት ነፍሰ በላ ሻለቆችንና የበታች መኮንኖችን «አገር አዳኑ» እያሉ ሲያሞካሹ የነበሩ ጉዶች ናቸው።

ፋሽስት ወያኔ ከነ ዘረኛ ደንቡ፣ ከነጉድፉ፣ ከነግሳንግሱና ግብስብሱ ተጠራርጎ እስካልተወገደ ድረስ ስር ተከል ለውጥ ለማምጣት ስንት መስዕዋትነት የተከፈለበት ሕዝባዊው ትግል አሁን እያየነው ባለው ሁናቴ አንድ ጥይት እንኳ ሳይተኩሱ ራሳቸውን እንደ ጀግና በሚቆጥሩ የራባቸውና ሁሉ ብርቁ ቀጣፊዎች መጠለፉ አይቀሬ ነው።

«ዓይኔን ሰው ራበው» የሚለው የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ግጥም ግጥሙ ከተገጠመለት ዘመን የልቅስ ይህን እያየነው ያለውን የዛሬውን ዘመን የሚገልጽ ይመስላል። ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ «ሰው በጠፋ ዘመን ባጉል ተወልጄ፣ ጅቡን አያ ጋሼ ቀበሮን ወዳጄ፣ እያልሁ እኖራለሁ በቤቴ በደጄ» እያሉ «ዓይኔን ሰው ራበው» የሚለውን ውስጥ ወይራና አስደማሚ ግጥማቸውን እንዲህ ያንቆረቁራሉ!

ዓይኔን ሰው አማረው፤ ዓይኔን ሰው አማረው፤ የሰው ያለህ የሰው! አያ ደሙ በኔ የሳጥናኤል መሪ፣ የቀበሮ እንግዳ በቤት አሳዳሪ፣ ተበግ ተቀበሮ ቀበሮን አክባሪ፣ ቀበሮን ወደ ቤት በግን ገደል መሪ፣ የበግ ለምድ ለብሶ በግን አባራሪ፣ በቀበሮው አዋጅ አገሩን ወራሪ፣ በለሰለሰ እርሻ አሜካላ ዘሪ፣ እጅግ ተጠንቅቆ አባቱን አፍቃሪ፣ አባቱን አፍቅሮ እናት አቃጣሪ፣ እናቱን አቃጥሮ አባት አሳሳሪ፣ አባት አሳስሮ በናቱ መስካሪ፣ በናቱ ላይ መክሮ አዋጅ አስነጋሪ፤ በግራ የቆመው ሲመለስ ወደ ቀኝ፣ እኔም በእናታችሁ ጎዳናው ሳይርቀኝ፣ በዚያን ጊዜ እናንተን የሚያይ ሰው ናፈቀኝ






Comments


bottom of page