የሰፋ ሀገር ይዘን ጠቦ መሞት ይብቃን
- አዳኙ ካሜራ

- Jan 6, 2019
- 1 min read
Updated: Jan 6, 2019
የሰፋ ሀገር ይዘን ጠቦ መሞት ይብቃን (ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ) -----------------------

አይችለው የለ እንጂ የልባም ትከሻ፣ ከውርደቱ ደጃፍ ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣ ገርፎ ማሳመን ነው የፈሪ ሰው በትር የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትህ አይታለምም ሀቁን እየሸሹ፣ የጠፋው እንዲገኝ እስኪ መጀመርያ ይፈተሽ ፈታሹ። አቀርቅራ ታዝግም ትጎናበስ እንጂ መሄድ እስኪያድላት፣ ሰብረህ ስታበቃ ምርኩዝ እንኪ ብለህ ደርሰህ አትደልላት። በኔ ብቻ በሽታ ጥበት እየቀጣን፣ በእናታችን እርስት በአባታችን መሬት መደገፊያ እያጣን፣ ቁልቁል እያሰቡ ምንድነው ከፍታ፣ መብት እየነጠቁ ምንድነው ግዴታ? እስከ መቼ ተረት ግዴለም ይነጋል፣ መንገድ እየቀሙ ምርኩዝ ምን ያደርጋል? አንተ እንደው ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ መግፋት፣ ካብኩ እያሉ ማቅለል ሳምኩ እያሉ መትፋት፣ የበደል ላይ ጀግና እሬሳ ላይ መዛት፣ መዋረድን ሽሽት የአሽቃባጭ አፍ መግዛት። እየሸሹ ትግል እየሮጡ ዛቻ፣ በጉንዳን ልቦና የነብር ዘመቻ። የበላ እያሰረ የቀማ ቢገፈው፣ የሳተ እያረመ ያጠፋ ቢገርፈው፣ ጀግና ልማዱ ነው ባርያ ሆኖ ታሽቶ ንጉስ ሆኖ መግዛት፣ እያነሰ ገዝፎ እየሞተ መብዛት። ያ ሽንታም ላመሉ በሬሳ ይፎክራል፣ ከፈሪ ገዳይ ድል የጀግና ሞት ያምራል።
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት የዘር ደዌ አያጥቃን፣ ከጎጥ ቀንበር ፍቱን ጠቦ መሞት በቃን። የጸደይ ወይን ሆኖ የሀቅ እንባ ቢጥም፣ በድሎ መጀገን ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣ የትግላችን ልኩ ያሳር ደም ቢያስምጥም፣ በሰፋ ሀገር ጠበን ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!



Comments