እምዬ_ምኒልክ_እና_እቴጌ_ጣይቱ_በገና_ጨዋታ
- አዳኙ ካሜራ

- Jan 6, 2019
- 1 min read
Updated: Jan 6, 2019

የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመን የገና ጨዋታ በታላቅ ድምቀት ይደርግ ነበር፡፡ በአንዱ የገና በዓል ላይም እንዲህ ሆኖ ነበር አጤ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ የየራሳቸውን ቡድን መስረተው በፍልውሃ ሜዳ ላይ የገና ጨዋታ ግጥሚያ ያደርጋሉ፡፡ በመጀመሪያው ቀን ጨዋታም የእቴጌይቱ ቡድን አሸናፊ ሆነ፡፡ በተለመዶው አሸናፊው ቡድን የተሸናፊውን ቡድን ማብሸቅ ያለና የነበር ቢሆንም የእቴጌ ጣይቱ ቡድን ግን ንጉሥን ፈርቶ ዝም አለ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ ነውና ሁኔታውን የተረዱት አጤ ምኒልክም "በሉ ስደቡን እንጂ አሉ" በዚህ ጊዜ "እጅ የለውም ወይ እጅ የለውም ወይ የምኒልክ ቡድን ሩር አይለጋም ወይ? ብርሌውን ብድግ ጠጁን ዶቅዶቃ የምኒልክ ቡድን ፍልውሃ ተወቃ" እያሉ ጨፈሩ፡፡ በማግስቱ በተደረገው ጨዋታ ግን "እጅ የለውም ወይ" የተባለው የአጤ ምኒልክ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ከዚያም "አረ ባየሽ አረ ባየሽ የኛ ጣይቱ አፍሽን በዳበሽ" እያለ በተራው ጨፈረ፡፡ በሕዝቡ ዘንድ የአጤ ምኒልክ ጥርስ ወደፊት ወጣ ያለ ነው እየተባለ ይወራም ስለነበር በዛው በገና ጨዋታ ላይ "ዘመዳዬ ዘመዳዬ በሰማይ የጠደቀ በምድር ያስታውቃል አቤቶ ምኒልክ ዘመዳዬ ተከንፈሩ ተርፎ ጥርሱ ጣይ ይሞቃል ዘመዳዬ አይክፋህ አብዬ ዘመዳዬ ጨዋታ ነው ብዬ፡፡" ተብሎ ተጨፍሮ ነበር፡፡


Comments