top of page

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ/ም

  • Writer: አዳኙ ካሜራ
    አዳኙ ካሜራ
  • Jan 6, 2019
  • 1 min read

Updated: Jan 6, 2019


የደርግ አባላት በታላቁ ኤዮቤልዩ ቤተመንግሥትን ተገኛተዋል እንደደረሱ ወደ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ቀርበው የያዙትን የደርግ ኮሚቴ ከስምምነት የደረሰበትን ደብዳቤ አውጥተው ለጆኖሆይ አንበቡላቸው ከሥልጣን ወርደዋል አሏቸው ጃኖሆይም እንዲህ አሉ የእኛ ታሪክ እዚህ ጋ ያበቃል የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ ዳርድንበሯን ማስጠበቅ ከአቃታችሁ ያንጊዜ የእናተ ታሪክ ይሞታል የእኛ ታሪክ ደሞ እንደገና ይጀምራል አሉ ጀኖሆይ:: ታላቁ ንጉሠነገሥት የታላቋ ኢትዮጵያ መሪ የተናገሩት አለቀረም ደርግ የኢትዮጵያን አርበኞችን ዲፕሎማቶችን ተማሪዎችን የመሬት ከበርቲዎችን በደርግ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ዙሪያ ጥያቄ ያላቸውን ሁሉ እየሰበሰበ ማሰር ማሰቃዬት ያለፍርድ መግደል ጀመረ ጃኖሆይ በስልትና በብለሃት ይዘውት የነበረውን የኤርትራን ጥያቄ በጦርነት ብቻ ለመፍታት ሞኮረ ህውሃት የተበለው የወንበዴ ቡድን ዳግማዊ ወያኔ ተብሎ ደደቢት ትግራይ ተመስርቶ ኢትዮጵያን ለመውጋት ሲዘጋጅ እነዚህን ወንበዴዎች ቀድመን ማጥፋት አለብን ብለው የኢትዮጵያ የጦር ጀነራሎች እና የሰራዊቱ አባላት ሲጠይቁት እነዚህን ተዋቸው ከፈለጉ በአንድ እስኪብርቶ እንፅፋልን በአንድ ጠረቤዛ ዙሪያ ተሰብስበን እንወያያለን እያለ ሲያሾፍ ወያኔ በበኩሉ ደርግ የሰጠውን ክፍተት ተጠቅሞ ለደርግ የጦር አመራሮች የተሳሳተ መረጃና ማስረጃ በሰውር እንዲደርሳቸው በማደረግ በመጀመሪያ በደርግ ውስጥ ያሉ የትግራይ ክፍለሃገር ተወላጆችን ከወያኔ ጋር በሚስጥር የሚሰሩ በማሥመሰል ለድርግ መረጃ በስጠት ህውሃት የትግራይ ክፍለሀገር ተወላጆዎችን አስገድሏል ሰኔ 15 ቀን 1981 ዓ /ም የሀውዚን ጭፍጨፋን ያስፈፀመው ህውሃት ነው መቀሌ ላይ ለአለው የኢትዮጵያ የጦር አዛዥ ሻምበል ነገሰ አስፋው የተሳሳተ መረጃ እንዲደርሰው በማድርግ ጀት አስነስቶ እንዲደበድብ በማድረግ ህውሃት ይህንን ድርጊት ለፖለቲካም ለወታደራዊም ጠቀሜታ አውሎታል ጎለያድ በትቢቱ ወደቀ ደርግም በትቢቱ ወደቀ እባቡ መርዛሙ ህውሃት በልቡ ተስቦ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ/ም አዲስ አበባ ሰተት ብሎ ገባ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር በመከፋፈል ለ27 አመት ገዛ መርዙ ከ27 አመት በሗላ እንኳን ከኢትዮጲያ ሊጠፋ አልቻለም::



Comments


bottom of page