የኢትዮጵያ ጀግና ደጅአዝማች ገረሱ ዱኪ
- አዳኙ ካሜራ

- Jan 6, 2019
- 1 min read
Updated: Jan 6, 2019
ሸዋ አንበሳ የኢትዮጵያ ጀግና ደጅአዝማች ገረሱ ዱኪ በ1928 ዓ/ም ጣልያን በኤርትራና በሱማሌ በኩል አድርጋ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት አድርጋ ለመግዛት ጦርነት ባወጀችበት ሰአት ጀግናው ደጅአዝማጅ ገረሱ ዱኪ በለባራስ ተብለው በራስ ካሳ ሀይሉ ጦር ስር ሆነው ትግራይ ጠቅላይ ግዛት በተንቤን ግንባር ተሰልፈው ደማቅ ታሪክ አኩሪ ገድል ከአስመዘጉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ጀግና ልጆዎች መካከል ደጅአዝማች ገረሱ ዱኪ የሳቱ ጉማጅ የአባ ጠቅ የጦር አበጋዝ አንዱ ነበሩ ጀግናው ደጅአዝማች ገረሱ ዱኪ የኢትዮጵያ ልጆዎች በተንቤን ግባር ተባብረው ሲዋጉ ተደራርበው ሲወድቁ የአዋጉም የተዋጉም ጀግና ነበሩ ጣልያን ኢትዮጵያን በጦር ሜዳ ተዋግታ ማሸነፍ እንደማትችል ስለተረዳች ኦሮሞና አማራን እርበርስ ለማጨራረስ ከራያ ከዋጅራት ከአዘቦ 35 ሺህ በንዳ ኦሮሞ ጣልያን መልምላ እርስበርስ ስታጨራርስ የተመለከቱት አንበሳውና ጀግናው ደጅአዝማች ገረሱ ዱኪ ከማይጨው ውጊያ በኇላ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ሸዋ እንደተመለሱ አዋጅ በማስነገር ጣልያን ኦሮሞ አማራን ግደል እኔ እረደሃለው ቢልህ እውነት አይምሰልህ እርበርሳችንን ሊያጠፈፉን ፈልገው ነው ለኦሮሞ አማራ ጠላቱ ሳይሆን ወንድሙ ነው የኦሮሞም ሆነ የኢትዮጵያ ጠላት እነዚህ ነጭ ሰይጣኖች ጣልያኖች ፋሺሽቶች ናቸው ሌላ ጣላት የለንም ጠላታችን ሰይጣኑ ጣልያን ብቻ ነው ሌላ ጠላት የለንም እኔን ተከተለኝ በማለት ስድስት(6)ሰዎች በማስከተን አበርበኝነትን አንድ ብለው ጀምረውታል አምስት (5) አመት ከወራሪው ጠላት ጋር ግባር ለግባር በመግጠም ተዋግተውና አዋግተው የኢትዮጵያን ጠላት የደመሰሱ ታላቅ ቆራጥ ጀግና አርበኛ ነበሩ ጀግናው ደጅአዝማች ገረሱ ዱኪ በወሊሶ ቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን እስከ ወዲያኛው ቢያንቀላፉም ደማቅ ታሪካቸው ህያው ምስክር ሆኖ ለዘለአለም ይኖራል:: ኢትዮጵያ በክብር ለዘለአለም ትኑር!!!

![የኦነግ ፕሮግራም አቀንቃኞች ወሎን ወይንም የጥንቱን ቤተ አማራ በሚመለከት የሚያስተጋቡት የፈጠራ ትርክታቸው ሲፈተሽ! [ክፍል ፩]](https://static.wixstatic.com/media/4e50d2_d90ccc98827f4c0ea08a5b7043ac0fe6~mv2.jpg/v1/fill/w_720,h_720,al_c,q_85,enc_avif,quality_auto/4e50d2_d90ccc98827f4c0ea08a5b7043ac0fe6~mv2.jpg)

Comments