የአክቲቪስቶቹ ነገር
- አዳኙ ካሜራ

- Jan 6, 2019
- 2 min read
Updated: Jan 6, 2019
የአክቲቪስቶቹ ነገር --- ገና የኦነግ አመራር ከአስመራ ከመምጣቱ በፊት ነበር "ኦነግ ከወያኔ ጋር እየሰራ ነው" የሚል ወሬ ማሰራጨት የጀመሩት። የኦነግ ጦር ከአስመራ በዘላምበሳ በኩል እንዲመጣ ሲታቀድ ደግሞ ግንባሩን በወጥመድ ውስጥ የሚከቱበትን ዘዴ ወጠኑ። ቁርስ በአዲግራት፣ ምሳ በመቀሌ የሚል ፕሮግራም ተወጠነ። ወያኔ በበኩሉ አሁን የሚጫወተውን ለኦነግ ያዘነ መስሎ ሌሎችን የማስደንገጥ ድራማ መተግበር ጀመረ።
ኦነግ ከስህተቱ የማይማር መሆኑ ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች ለሚጫወቱት ድራማ ተመቻቸው። ለምሳሌ የኦነግ ሰዎች ኦቦይ ስብሐት የኦሮሞን ባንዲራ ይዘው ፎቶ መነሳታቸው በህብረተሰቡ ዘንድ የሚፈጥረውን አሉታዊ ስሜት አለመረዳታቸው ዛሬም ከስህተት አለመማራቸውን የሚገልጽ ነበር። በዚያች ባንዲራ የተጀመረው ኦነግን የማጥቆር ተውኔት አምሮና ጎልብቶ ዛሬ "አባቶርቤ ሊገድለኝ ነው፣ በየጊዜው የሞት ዛቻ ይደርሰኛል" ከሚል የclimax ደረጃ ላይ ደርሷል። ---- እነዚህ አክቲቪስት ተብዬዎች እይታቸው እንደ እንቁራሪቷ ነው። የዛሬውን እንጂ የነገውን አሻግረው አያዩም። የነርሱ እርካታ ዝና፣ ጥቅም እና የስልጣን ጥምን መወጣት ነው። ከዚያ ባለፈ በሁለቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መካከል የሚካሄድ ግጭት ወደፊት የሚያመጣውን አሉታዊ ውጤት ማየት አልፈለጉም።
# ኦነግና እና ኦዴፓ ቢዋጉ የወደፊቱ የኦሮሚያ ሰላምና ደህንነት እንዴት ሊሆን ይችላል? # ድርጅቶቹ ቢዋጉ የኦሮሞ ህዝብ አንድነት ምን ሊሆን ይችላል? # መጪው ትውልድ ከዚህ ግጭት ምን ይማራል? # የድርጅቶቹ መዋጋት በታሪክ ፊት የሚሰጠው ፍርድ ምን ዓይነት ነው? # ወዘተ ወዘተ ወዘተ ---- ባለዲግሪ እና የፖለቲካ ተንታኝ ነኝ የሚል ሰው ነገሮችን ከብዙ አቅጣጫ ነው የሚመዝነው። አሁን እየተደረገ ያለው ግን "ኦነግን በቅድሚያ በፕሮፓጋንዳ ሞገድ ከበከሉ በኋላ ግንባሩን በጦር ሃይል አሳድዶ ማጥፋት ይቻላል" የሚል አካሄድ ነው።
በ1984 ወያኔ አድርጎት አይተነዋል። ግን አልሰራለትም። በ26 ዓመቱ ከባድ ዋጋ አስከፍሎት ከስልጣን አስወግዶታል። የአሁኑ ደግሞ ለዚያም የሚያደርስ አይደለም። ምክንያቱም ግጭቱ የሚካሄደው በሁለት የኦሮሞ ድርጅቶች መካከል ነውና። --- ኦቦ ለማንና ዶክተር አቢይን የሚደግፍ ሰው ጦርነት አይመኝም። ፍጥጫውን በጦርነት ማገባደድ ወደ ሌላ አዙሪት ነው የሚከተን።
ስለዚህ በአማካሪነት ስም ከውጪ መጥታችሁ በኢሊሊ ሆቴል መሽጋችሁ ይህንን የጥፋት ድግስ ለኦሮሞ ህዝብ የቀመራችሁ ሰዎች የሰላም አቅጣጫን ያዙ። ከሽማግሌዎች ጋር ተባበሩና ፍጥጫውን በሰላም ለመፍታት ሞክሩ። አለበለዚያ የተበከለ ታሪካችሁን እንደምናጋልጥ እወቁ (ለምሳሌ አንደኛው ሙስኬቶ አክቲቪስት ነኝ ባይ የዶክትሬት ዲግሪ ሳይኖረው "ዶክተር ነኝ" ይላል)። ----- ለኦነግ እና ለኦዴፓ አመራሮች
ችግሮቻችሁን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ፍቱ። አባገዳዎች ያቀረቡትን የመፍትሔ ሐሳብ ተቀበሉ። የኦሮሞ ህዝብ አንድነትን አትበትኑት። ተጠንቀቁ።




Comments